በዚያን ጊዜ ነው በአስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር የተሰራው ታላቁ የኢሠፓ የጉባኤ አዳራሽ ተመርቆ የተከፈተው፡፡ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት ያለው የ“ትግላችን” ሀውልትም በዚህ በዓል ወቅት ነው የተመረቀው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለበዓሉ የታጨችው አዲስ አበባ በደማቅ መብራቶችና በልዩ ልዩ መፈክሮች ተጥለቅልቃ ነበር፡፡ እንግዶች በሚንቀሳቀሱባቸው ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ያሉ አሮጌ ቤቶች በግንብ አጥርና በትላልቅ የጨርቅ ሽፋኖች እንዲከለሉ ተደርገዋል Continue reading